አለም ወደ አንድ መንደር በመጣችበት በዚህ ጊዜ ሀገራችን ኢትዮጵያ ካደጉት ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ ዘርፌ ብዙ ተግባራትን በቴክኖሎጂ ዘርፍ በማከናወን ላይ ትገኛለች፡፡ ዳውሮ ዞን በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ ውስጥ ካሉት ዞኖች አንዱ ሲሆን በውስጡ የያዛቸው የተፈጥሮ ሀብት፣ባህልና ቅርስ አስተሳስሮ ለዓለም ህብረተሰብ ለማስተዋወቅ ብሎም የዲሞክራሲ፣የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን በቴክኖሎጂ አስደግፎ ተደራሽ ለማድረግ የድህረ- ገጽ ልማት ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡
በመሆኑም ዞናችን ይህንን ድረገጽ በማልማት የተፈጥሮ ሀብቶቻችንን፣ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎችን፣ የመንግስት የዲሞክራሲ፣የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ቴክኖሎጂን መጠቀም ለተገልጋዩ ህብረተሰብና ለዓለም ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ በየደረጃው ካለው ባለቤትና ባለደረሻ አካላት በሁለት አመታት ውስጥ ሰፊ ጥረቶች ተደርጓል:: ስለሆነም የዞናችንን ድረገጽ በመጎብኘት መረጃ ማግኘት፣በመጎብኘትና ኢንቨስት በማድረግ ሀገርዎንና ራስዎን ተጠቃሚ እንዲያደረጉ ጥሪ እናቀርባለን::