ዌብሳይት

የዳዉሮ ዞን ሣይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ በዞኑ ሁለት ዌብ ሣይቶችን መክፈቱን ገለፀ።
የመምሪያ ኃላፊ የሆኑ ወ/ሮ ቤተልሔም ዳንኤል ይህ ድህረ-ገጽ የዞናችንን መልካም ምድር እና ገጸ በረከቶችን ለዓለም ህዝብ በማስተዋወቅ ከፍተኛ ምና በመኖሩና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመረጃ ሥርዓትን ለማስፋት ምቹ ሁኔታየሚፈጥር መሆኑን ገልፀዋል።
በቅርቡ የባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና የቴክኖሎጂ ኢኖቬሽን በጋራ ያዘጋጁቶት ቨርቹዋል 360 ቱር አፕሊኬሽን መመረቁን የጠቀሱት የዳዉሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተክሌ በዛብህ በዞን ደረጃ የተዘጋጁት ሁለት ዌብ ሣይቶች በወቅታዊና በቂ መረጃዎች እየበለፀጉ መሄድ እንዳለባቸዉ ገልፀዋል።
ድረገጹን በማልማት የተፈጥሮ ሀብቶቻችንን፣ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎችን፣ የመንግስት የዲሞክራሲ፣የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ቴክኖሎጂን መጠቀም ለተገልጋዩ ህብረተሰብና ለዓለም ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ በየደረጃው ካለው ባለቤትና ባለደረሻ አካላት በሁለት አመታት ውስጥ ሰፊ ጥረቶች መደረጉን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪዉ የዞኑን ድረገጽ በመጎብኘት መረጃ ማግኘት፣በመጎብኘትና ኢንቨስት በማድረግ ሀገርዎንና ራስዎን ተጠቃሚ እንዲያደረጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ዘገባዉ የዳዉሮ ዞን መንግስት ኮሚንኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ።

news & events image: