ታሪካዊው ሀላላ ድንጋይ ካብ

  • በዳውሮ ታሪክ ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው የሀላላ ድንጋይ ካብ የተገነባው በ16ኛው  ክፍለ ዘመን ከውጪ ወራሪ ኃይሎች ዳር ድንበሩን ለመጠበቅና ራሱን ከጠላት ለመከላከል የኦሞንና የጎጀብ ወንዝ ተፋሰስ ተከትሎ ውፍረቱ 3.5 ሜ፣ ቁመቱ 2-3ሜ፣ ከ3 እስከ 7 ዙር የታጠረ/የተገነባ/ ሲሆን የአንዱ ረድፍ ርዝመት 175 ኪ.ሜ ነው፡፡ የዞኑ ቆዳ ስፋት 4461 ካሬ ኪሎ ሜትር ነው፡፡ ይህንን የሚሸፍነውን የዳውሮ ዙሪያውን በማካለል የተገነባው የንጉሥ ሀላላ ድንጋይ ካብ 7 መግቢያ በሮች/ሚፃዎች አሉት፡፡ እነሱም፡-የየሊ በር፣ የዚማ በር፣ የዛባ በር፣ የጋራዳ በር፣ የዳራ በር፣ የአባ በር እና የቃሎ በር በመባል የሚታወቁና ንጉሡ በመረጣቸው ተሿሚዎች ሚፃውን ያስጠብቃሉ፡፡
  • ካቡን ልዩ የሚያደርገው፡- ካለ ምንም አሸዋና ሲሚንቶ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ተነባብሮ የቆመና 400 ዓመት በፊት በጥበባዊ ይዘት በድንጋዮች መጠንና በአደራደሩ ረቂቅ ስልት መገንባቱ፣ በዓለም የመንግስታት ታሪክ የግዛቱን ዳር ድንበር ከጠላት ጥቃት ለመከላከል በጠንካራ ግንብ መሪው ሲገነባ ለቀረው ዓለም መልካም አርአያነቱና የጎበኚን ቀልብ በመሳብ ገቢ ሊያስገኝ የሚያስችል መሆኑ፣ የህብረተሰብ ጥንታዊ የሥነ-ህንፃ ዲዛይን ያለው ታሪካዊ አሻራ ሆኖ እስከ ዛሬ ድረስ ሳይፈርስ መገኘቱ፣ የድንጋይ ካቡ ተጀምሮ የተጠናቀቀበት ጊዜ ህብረተሰቡ ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ አኳያ የዳውሮ ህዝብ ለሀገሩ ያሳዩት ከፍተኛ  ተቆርቋሪነትና የሥራ ጥንካሬን የሚያሳይ መሆኑ፣ በወቅቱ ከነበሩ የአካባቢ አውራጃዎች/የአሁኑ አጎራባቾች/ ዞኖችን  የሚያገናኝ ሰባት ዋና በሮች በመሪው በተሾሙ የጦር መሪዎች የሚጠበቁ መሆኑ፣ የኦሞን ወንዝ ተከትሎ ነጭ የእጣንና የሙጫ ዛፍና በርካታ ፍል ውኃዎች መገኘቱ ፣ ታሪካዊ ካቡ ዙሪያ ተፈጥሮአዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ የቱሪስት መስህቦች እና ለኢንቨስትመንት ሊውሉ የሚችሉ አያሌ ሀብቶች  በአካባቢው መታየቱ፣ የዞኑን ዳር ድንበር ከጠላት የፈረሰኛ ጦር ከመከላከል ውጪ የግንባታው አፈጻጸም የተፈጥሮ ውበትን በዘላቂነት ለማቆየት ለጎርፍ አደጋ በዘመናዊነት ከሚመከረው የተፋሰስ ሥራ አንዱ በመሆኑ አፈርን በማቆየት አርሶ አደር የእርሻ ውጤቱ እንዲቋደስ  መርዳቱ፣ ለአዲሱ ትውልድ ምርጥ ተሞክሮ መሆኑ ቅርሱን ለየት ያደርገዋል፡፡
  • የአካባቢውን ውበት ይበልጥ የሚያጎለው ለአየር ንብረት ሚዛንን ላለመንካትና ኃይል ምንጭነት የተገደበው የጊቤ 3 ኤለክትሪክ ሀይል ማመንጫ ግድብ  ምክንያት የሚፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ በተለይ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለዓሣ ሀብት እርባታ፣ ለጀልባ አገልግሎት፣ የአካባቢውን ውበት ለማድነቅ ለሚመጡ ተገልጋዮች አስጎበኚ ማህበራት የባህላዊ ሎጂ፣ ሪዞርት ግንባታ ለማካሄድ ሚቹ ቦታ ከመሆኑም በላይ የመንገድ መሠረተ ልማት መኖሩ፣ ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ግብዐት የሚሆኑ ሽፋራው‹ሀላኮ›፣ አቮካዶ፣ ቡርቱካን፣ ሎሚ፣ ሙዝ፣ ፓፓያ፣ ኦቾሎን፣ ካሳቫ፣ ጤፍ፣ እንስሳትና የእንስሳት ውጤቶች በስፋት መብቀሉና መኖሩ  ቅርሱ/ሀብቱ/ በህብረተሰቡ ጥያቄና በዞኑ መስተዳደርና በክልሉ መንግስት ተሳትፎ በፌደራል የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን በሀገር ቅርስነት ተመዝግቦ እውቅና መሰጠቱ፣ ቅርሱ አሁን ላለው ትውልድ ለማሳወቅና ለመጪውም ለማስተላለፍ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ጥረት እየተደረገ መሆኑ  ካቡን ይበልጡን ለማስተዋወቅና ለማልማት ሚቹ ዕድል ስለሆነ ኢንቨስት በማድረግ፣በመጎበኚት፣ በመዝናናትና ምርምር በማካሄድ ድርሻዎን  እንዲወጡ ተጋብዘዋል፡፡
TourisimSlideshowblockImage: