ማሎ ዋሻ

ማሎ ዋሻ በቶጫ ወረዳ በመድኃነዓለም ቀበሌ ውስጥ በደል ንኡስ  ከዞኑ ርዕሰ ከተማ ታርጫ በስተደቡባ ምዕራብ 42 .ሜትር ላይ ይገኛል፡፡ ከቶጫ ከተማ በስተሰሜን 2 .ሜትር ላይ የሚገኝ ሲሆን ቦታው በተሽከርካሪ ለመሄድ አመቺ ቢሆንም እንደአማራጭ በእግር የአካባቢውን ተፈጥሮ የሕዝቡን ሰፋፈርና አኗኗር እየቃኙና ተደነቁ በቀላሎ ወደ ቦታው መድረስ ይቻላል፡፡ ዋሻ መገኛ በካርታ ሲናይ Latitude   070051 54.311 Northing Latitude Longitude  0340 02145.411   Easting longitude   ከፍታው ከባህር ጠለል በላይ /Height above sea level /2675 ነው፡፡ ይህ ዋሻው በተራራው  መካከለኛ  ክፍል ላይ በመሆኑ ወደ ዋሻው በር ለመድረስ 60 ሜትር ያህል  አስቸጋሪ  በመሆኑ  ወደ  ገደሉ ተንሸራተው እንዳይወድቁ  ጥንቃቄ የተሞላበት  አካሄድን ይጠይቃል፡፡ እንደምንም ዋሻው በር ከደረሱ በኋላ አስደናቂና አስገራሚ የሆነውን ሰው ሰራሽ ዋሻ መግቢያ በር መመልከት ይጀምራሉ፡፡ የበሮቹ አሠራር ከፊል የክብ ቅርፅ ያላቸው የፊተኛ መግቢያ በር እና የኋለኛው መግቢያ በሮች አለው፡፡ የበሮቹ ስፋት 95 .  ራዲየስ ነው፡፡  አጠቃላይ  ዋሻው የውስጥ ወለል ስፋት ሶስት ሜትር በሁለት ሜትር የሆነ ነው፡፡  ከወለል  እስከ   ጣሪያው ያለው ቁመት አንድ  ሜትር  ተኩል ሲሆን በውስጠኛው ክፍል በተለያዩ ቅርፅ የተቦረቦረ ዕቃ ማስቀመጫ መደሪደሪያ መገኘቱና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሰዎች ይጠቀሙበት የነበረው የቤት ቁሳቁሶች ቀሪት አካል እንደነበረ የአካባቢው ህብረተሰብ ይናገራሉ፡፡ ይህንን መረጃ ስንሰጥዎ እንደምትጎብኙ በመተማመን ነው፡፡


TourisimSlideshowblockImage: