Welcome to XAMPP for Windows

ፓርኩ የተመሠረተውም በክልሉ መንግስት አማካይነት 1997 ዓ.ም የአካባቢው ህብረተሰብና የአስተዳደሮች ጥያቄና ተሳትፎ በመከለሉ ከማንኛውም ሥጋት ነጻ በመሆን ለብዝኃ- ሕይወትና ለዱር እንስሳት ምቹና አስተማማኝ የጥበቃ ቦታ በመሆኑ በክልል ደረጃ የ2007 ዓ.ም አፈጻጸም ተገምግሞ 1ኛ ደረጃ በማውጣት ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ቅርሱ የሚገኘው በመካለኛው ከኦሞ ሸለቆ ተፋሰስ በዳውሮ ዞን በኩል ከቶጫ ወረዳ (ማሊጋ ማራጫ፣ ማንታ ጉቺልና ሙጋ ቀበሌያት)፣ በኢሠራ ወረዳ (አዳ ባቾ፣ ጩርጩራ፣ ጫውዳ፣ ጉዱሙ፣ ቡባ ይልጋ፣ ናዳ  ቀበለያትን በማቀፍና በኮንታ ልዩ ወረዳ የሚገኝ ሲሆን የቆዳ ስፋትም 1190 ካሬ ኪሎ ሜትር፣ ከፍታውም ከባህር ወለል በላይ ከ700ሜ እስከ 2800ሜ መካከል ይገኛል፡፡ በአካባቢው ከመጋቢት እስከ መስከረም አንዳንድ ቦታ እስከ ታህሳስ የሚዘልቅ ረጅምና ወጥ የሆኑ ዝናብ የሚገኝ ሲሆን ሀምሌና ነሐሴ ወራት ከፍተኛ ዝናብ የሚታይበት ነው፡፡ ጥርና የካቲት የሙቀት ወቅቶች ሲሆን ፓርኩ የተለያዩ የውኃ ተፋሰሶች ማለትም ወንዞች፣ ጅሬቶችና ሀይቆችን ያቀፈ በመሆኑ ብዛት ያላቸው የዱር እንስሳት እንዲርመሰመሱ ምክንያት ሆኗል፡፡ ታላቁ የኦሞ ወንዝ የፓርኩን ደቡባዊ ክፍል የሚያዋስን ሲሆን ሌሎቹ ፓርኩን አቋርጠው የሚያልፉ ቋሚና ገባር ወንዞች፡- ዚጊና፣ ሾሹማና፣ አድኮላ ዋና ዋና ናቸው፡፡ በተጨማሪ ጮፎሬ፣ሙንኦ ዎንባ፣ ካርቤላ፣ ሺሻ፣ ዶኖ ዎንባ ሀይቆች ይገኛል፡፡