የቱሪዝም ኢንዱስትሪ

የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ግዙፍና ከጊዜ ወደ ጊዜ ፈጣን  ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በማንቀሳቀስ በዓለም ኤክስፖርት ንግድ ቀዳሚ ስፍራ የያዘ፣ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት የውጪ ምንዛሪ ምንጭ የሆነ፣ የአነስተኛ መካከለኛና ከፍተኛ ኢንተርፍራይዞች ዕድገት የሚያግዝ፣ ከፍተኛ የሆነ የሥራ ዕድል የሚፈጥር፣ የባህላዊ ታሪካዊና የተፈጥሮ ቅርሶች ለመጠበቅ ከፍተኛ ሚና ያለው ዘርፍ ነው፡፡

ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ ግብዓትነት ሊውሉ የሚችል፡- ተፈጥሮአዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ ሀብቶችንና  የቱሪዝም ምርት ሆነው ሊቀርቡና ለማምረት የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎች ሲሆን ምርት የሚባሉት የለማ መስህብ፣ የጉብኝትና የመስተንግዶ አገልግሎት፣ ዕድ ጥበብ ውጤቶች፣ ወዘተትስስር ያለው ነው፡፡

ተፈጥሮአዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ መስህቦችን የአንድ ህዝብ በጊዜ ብዛት የፈጠራቸው፣ያለማቸውና ጠብቆ ለዚህ ዘመን ያደረሳቸው ሀብቶች ሲሆኑ ያላቸውን ማህበራዊ፣ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያ ፋይዳ ለማስቀጠል ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ ይጠበቃል፡፡  ቱሪዝም ኢንዱስትሪ በእነዚህ ሀብቶች አካባቢ የሚኖረውን ህዝብ ማህበረ ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የባለቤትነት ስሜት በመፍጠር ለጥበቃው፣ ለልማቱ፣ ለግብይቱ አጋዝ ኃይል ነው፡፡

ኢንዳስትሪውን በላቀ ፍጥነት እንዲያደግ ከሚያስችሉና በየቦታው የሀገር ቅርስ ሆነው ያልታወቁ ውበት በዚህ ፅሁፍ ይዳሰሳል፡፡

በዳውሮ ዞን ውስጥ ያሉ ተፈጥሮአዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ መስህቦች በጥቅሉ ቀልብ ከሚስቡ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ በተለይም 500 ከባህር ወለል በላይ  ኦሞንና ዚግና ወንዝን መነሻ በማድረግ እስከ 2820 ከፍታ ቦታ ቶጫ ቱታ ተራራ ድረስ በሦስት አየር ቀጠናዎችን በማካተት  ደጋ 21%፣ወይና ደጋ 41% ቆላ 38%  ይዟል፡፡ በተለያዩ አካባቢ የቅመማ ቅመም ሰብሎች (ኮረርማ፣ ዝንጅብል፣ ጥምዝ ወዘተ…) የተፈጥሮና  ሰው ሰራሽ ደን(ሶሎ፣ጎጋሮ፣ ጉዳ፣ ፃኪ ያማ፣ ቤራ፣ ኩሙኩማ፣ ሳዮ ወዘተ… ) ጨበራ ጩርጩራ /ፓርክ፣ በአገር በቀል ዛፎች የተዋቡ ተራራዎች (አጦ፣ ጋዞ፣ ኢሠራ፣ ቱታ፣ ገቤሮ፣ ሳዳማ ወዘተ.. )፣ከፍተኛ ፍሰት መጠን ያላቸው ወንዞች (ኦሞ፣ ጎጀብ፣ ዞአ፣ ባጭሬ፣ ካሬታ፣ ሻታ፣ ሼፓ፣ ወጋዬ፣ ማንታ፣ ዝግና፣ ፋንታ፣ ኮማ ወዘተ…) በርካታ የውስጥ ደዌና የቆዳ በሽታ በመፈወስ እና ለእንስሳት እርባታና ድለባ የሚያገለግሉ ሆራ ማዕድናትን የያዙ እና  የእንሰሳትና የሰው ሆስፒታል በመሆን የሚያገልግሉ ታዋቂ ፍል ውኃዎች (ሺቃ፣ ሶግዳ፣ ሶቦ፣ ዳራ፣ ቂምባ፣ ቦዶላ ማማዶ፣ ወዘተ…) ለአርኪዮሎጂና ለአንትሮፖሎጂ ምርመሮች እጅግ ተፈላጊ የሆኑ ዋሻዎች(ካቲ ሁሉቁዋ፣ ሻሌ፣ ያኮ መንትያ፣ ዎኖ፣ ሻሊ ጋዎ፣ ማሎ፣ ጋማሪ፣ ቶሞሶ፣ ወዘተ…) ረዣዥም ፏፏቴዎች (ኮራንቶ፣ ኮቶሮ፣ ውኒ፣አል ወዘተ..)፣ውድ የሆኑ ማዕድናት(ወርቅ አፈር፣ ብረት አፈር፣ ድንጋይ ከሰል፣ እምነ በረድ፣ ሬድ አሽ ወዘተ፣.. ) ታሪካዊ ቦታዎችና የድንጋይ ካቦች ከላይ የተጠቀሱትና ያልተጠቀሱ  ሀብቶች በአጠቃላይ  በዞኑ ቆዳ ስፋት 446082 ሄክተር ውስጥ የሚገኙ የሀገር ቅርሶች ናቸው፡፡

ለዞኑ ከታደለው የተፈጥሮና ብሔራዊ ቅርስ ከሆነው ከጨበራ ጩርጩራ /ፓርክ ሲንጀምር ይህ ፓርክ በውስጡ እምቅ ብዝኃ ህይወት ያለው ውብ እና በአለም ዝሪያው በመመናመን ላይ የሚገኘውን የአፍሪቃ ዝሆንና ሌሎች ብርቅዬና  ድንቅ የሆኑ እንስሳትና አዕዋፋት መገኛ በመሆን ይታወቃል፡፡ የተመሠረተውም በክልሉ መንግስት አማካይነት 1997 . የአካባቢው ህብረተሰብና የአስተዳደሮች ጥያቄና ተሳትፎ በመከለሉ ከማንኛውም ሥጋት ነጻ በመሆን ለብዝኃ- ሕይወትና ለዱር እንስሳት ምቹና አስተማማኝ የጥበቃ ቦታ በመሆኑ በክልል ደረጃ 2007 . አፈጻጸም ተገምግሞ 1 ደረጃ በማውጣት ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ቅርሱ የሚገኘው በመካለኛው ከኦሞ ሸለቆ ተፋሰስ በዳውሮ ዞን በኩል ከቶጫ ወረዳ (ማሊጋ ማራጫ፣ ማንታ ጉቺልና ሙጋ ቀበሌያት) በኢሠራ ወረዳ (አዳ ባቾ፣ ጩርጩራ፣ ጫውዳ፣ ጉዱሙ፣ ቡባ ይልጋ፣ ናዳ  ቀበለያትን በማቀፍና በኮንታ ልዩ ወረዳ የሚገኝ ሲሆን የቆዳ ስፋትም 1190 ካሬ ኪሎ ሜትር፣ ከፍታውም ከባህር ወለል በላይ 700 እስከ 2800 መካከል ይገኛል፡፡ በአካባቢው ከመጋቢት እስከ መስከረም አንዳንድ ቦታ እስከ ታህሳስ የሚዘልቅ ረጅምና ወጥ የሆኑ ዝናብ የሚገኝ ሲሆን ሀምሌና ነሐሴ ወራት ከፍተኛ ዝናብ የሚታይበት ነው፡፡ ጥርና የካቲት የሙቀት ወቅቶች ሲሆን ፓርኩ የተለያዩ የውኃ ተፋሰሶች ማለትም ወንዞች፣ ጅሬቶችና ሀይቆችን ያቀፈ በመሆኑ ብዛት ያላቸው የዱር እንስሳት እንዲርመሰመሱ ምክንያት ሆኗል፡፡ ታላቁ የኦሞ ወንዝ የፓርኩን ደቡባዊ ክፍል የሚያዋስን ሲሆን ሌሎቹ ፓርኩን አቋርጠው የሚያልፉ ቋሚና ገባር ወንዞች፡- ዚጊና፣ ሾሹማና፣ አድኮላ ዋና ዋና ናቸው፡፡ በተጨማሪ ጮፎሬ፣ሙንኦ ዎንባ፣ ካርቤላ፣ሺሻ፣ ዶኖ ዎንባ ሀይቆች ይገኛል፡፡

ፓርኩ በሰሜን ምስራቅና በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ ሰንሰለታማ ተራራዎች የተከበበና በውስጡ ብዛት ያላቸው ትላልቅና አነስተኛ ኮረብታዎች፣ሜዳማ መሬቶች፣ ሰፋፊ ሸጦች፣ ረዣዥም ሳቨና፣ ሣር ለበስ መሬት፣የአገር በቀል ዛፎች፣ የወንዝ ዳር ደኖች፣ ጥቅጥቅ ያሉ የእንጨት ለበስ ደኖች፣ በደን የተሸፈኑ ተራራዎች የያዘ ነው፡፡ 

በብ/ፓርክ ውስጥ ያሉ ዱር እንስሳት በተለያዩ ጊዜያት በተደረገው ቆጠራ መሠረት 37 ትላልቅና መካከለኛ የአጥቢ ዝሪያዎች፣ 237 የአዕዋፋ ዝሪያዎች እና በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ አምስት የአዕዋፋት ዝሪያዎች ተመዝግበዋል፡፡ በአጥቢ ዱር እንስሳት በኩል ዝሆን፣ ጎሽ፣ ጉማሬ፣ ብኾር፣ ከርከሮ፣ ድኩላ፣ ድፋርሳ፣ ትልቁ አጋዘን፣ አሳማ፣ ዝንጆሮ፣ ጦጣ፣ አንበሳ፣ ነብር፣የዱር ድመት፣ አነር ወዘተበቀላሉ የሚጎበኙ ናቸው፡፡ ይህን ድንቅ የሆነውን ፓርክ ለመድረስ ከአዲስ አበባ-- ሶዶ-- ዋካ-- ቶጫ ወይም   ከአዲስ አበባ-- ጂማ-- ጭዳ- አማያ መንገድ መጠቀም ይቻላል፡፡ የፓርኩን ገፅታ የሚያሳይ በተወሰነ መልኩ የበጋ መንገድ ያለ ሲሆን በፓርክ ውስጥ የተለያዩ መስህቦችን ለመጎበኝት የውስጥ ለውስጥ መንገድ በመጠቀም በቱሪስት መኪና፣ በእግር፣ በፈረስና በበቅሎ እየተዘዋወሩ መመልከት ይቻላል፡፡

በተጨማር በአካባቢ የሚታዩ ሀብቶች ጥንታዊ የቶጫ መድኃነዓለም ቤተ ክርስቲያን እና ኢሠራ ባለ /ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን  ብዙዎችን የሚስቡ  ጥንታዊ የሀይማኖት ቦታዎች ናቸው፡፡  ስለሆነም ማናኛውም ሀገሩንና አካባቢን በመጥቀም ለራሱም እጠቀማለሁ የሚል አልሚ ባለሀብትን ዞኑ እጆቹን ዘርግተው በናፍቆት እየጠበቀ ባለሀብቱም በሆቴል፣ በሎጅ፣ በአስጎበኚነት እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት  ዘርፍ ቢሰማራ ውጤታማ እንደሚሆኑ እንመክራለን፡፡