ኮራንቶ ፏፏቴ

 

ኮራንቶ ፏፏቴ፡- ፏፏተው ከአሰገራም ተፈጥሮ በግምት 150 . በላይ ከፍታ የሚወረድ ለውቧ ዳዉሮ ተፈጥሮ የቸረላት ቱሪስት መዳረሻ ለጎበኚ ወይም ለተመራማር ልዩ ስሜት የሚፈጥር ማራኪ ምድረ-ገነት ተምሳሌት ፏፏቴ ነው፡፡ የሚገኘውም በሎማ ቦሳና ዲሣ ወረዳ መካከል ከገሣ 22 .ሜ ርቀት በሚዳ-ዛሎና በኮይሻ ማህበረሰብ ተጠብቆ የቆየ ቱሪዝም ሀብት ነው፡፡ በቱሪስት የሚጎበኝ ቀልብ የሚስቡ ለሎች መዳረሻዎች በአቅራቢያው ተያያዥ መስህቦች፤ባሌሰንሰለታማ ተራራ፤ የማታ ጥብቅ ደን፣ ያኮማንቲያ ዋሻ ታሪካዊ ይሁን ተፈጥሯዊ ብዙ ጥናትና ምርምር ሥራ የሚፈልግ ድንቅ ዋሻና ታሪካዊ"ሁሉቁዋ"ዋሻ የዳውሮ ንጉስ የማንጻት ሥነ-ሥርዓት የሚየስፈጽምበት ዋሻ ነው፡፡ በዋሻው የባህላዊ እምነት በመጣስ ግብረ-ሥጋግንኙነት ፈጽሞ የተገኘ ሰው ኃጢአትና ሌሎች በባህሉ እርኩሰት ነው የተባሉ ድርግቶችን የማንጻት ሥነ-ሥርዓት ክንዋኔዎች በዳወሮ ነገስታቶች ሥር የት የሚጸምበት መግቢያና መውጫ ያለው ድንቅ ዋሻ ፍፁም ታሪካዊ በሚሰጥ ተፈጥሮ የታጀበ ድንቃድንቅ ስፍራዎችን በአንድ ጉዞ የሚጎበኚ በመሆኑ መሰህቦቹ ለቱሪስቶች ተመራጭ መዳረሻ ናቸው፡፡