ካቲ ሁሉቆ ዋሻ

ካቲ ሁሉቁዋ በዞናችን ውስጥ በሎማ ወረዳ የሚገኝ ታሪካዊ ዋሻ ነው፡፡ ካቲ ሁሉቁዋ የማንፃት ዋሻ ስሆን ይህ ታሪካዊው ዋሻ ከዛሬ 400 ዓመታት በፍት እንደተሠራ የአከባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ ዋሻው የመግብያና መውጫ በር ያለውና የዳውሮ ንጉስ የነበሩ የካቲ ሃላላ ባህላዊ የማንፃት(healing service) ሥነ-ሥርዓት ያከናወኑበት ዋሻ ነው፡፡ የዋሻው የላኛው መግቢያ በር ስፋቱ 29 ሜትር ቁመቱ ደግሞ 12 ሜትር ነው፡፡ የታችኛው መውጫ በር ደግሞ መዳማ ሆኖ ስፋቱ 46 ሜትር ቁመቱ ደግሞ 21 ሜትር ነው፡፡ ውስጥ ለውስጥ 69 ሜትር ርዝሜት ስኖረው ከአንዱ ግድግዳ እስከ ሌላው ያለው የውስጥ ስፋት 28 ሜትር ነው፡፡ ከወለሉ እስከጣራው ደግሞ 7 ሜትር ርዝሜት ርዝሜት አለው፡፡