ታሪካዊው ሀላላ ድንጋይ ካብ

የንጉስ ሀላላ ድንጋይ ካቢ፡- በአጠቃላይየዳውሮን ዳር ድንበር ከ3 ዙር እስከ 7 ዙር የተገነባ የአንድ ረድፍ ርዝመት 175 ኪ/ሜትር ስሆን ውፍረቱ ከ2.5 እስከ 5 ሜትር የሚደርስ የድንጋይ ካቢ ቁመት አማካይ ከ2.5 እስከ 3.8 ሜትር የሚደርስ ርዝማኔ ያለው፣ የስነ-ህንፃ ጥንት የዳውሮ ህዝብ በሰባት በሮች የሚመጡብንን የጠላት ጦር ጥበቃ መከላከያ ታሳብ ተደርጎ የተገነባ የድንጋይ ካብ ነው፡፡ የድንጋይ ካቢ ታሳቢ ከጠላት ኃይላት መከላከል ብቻ ሳይሆን የመሬት መሻራሸር ጥበቃ ቴክኖሎጅ ሥልጣኔ መሠረት ከሀገር በቀል ዕውቀት ከአለት ተፈልፍሎ በ16ኛው ክ/ዘመን ተጀምሮ በ18ኛው ክ/ዘመን መጀመሪያ የተጠናቀቀ የድንጋይ ካቢ ነው(አድማሱ፡ 2003፣ ፃዲቁ፡ 2011)፡፡ ይህን ግንብ ወይም ካቢ ሥራ የሰባት ወራባ ግዛት ነዋሪ ህዝብ ከ20 እስከ 25 ዓመት በላይ ጊዜ የፈጀበት መሆኑን በብዙ ታሪክ ፀሐፊዎችና ለሀገርና ለውጭ ሀገራት ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ ነው፡፡ በጀግንነት የራሱን ዳር ድንበር ከጠላት ወረራና ጥቃት ለመከላከል በንጉስ ሀላላ የግዛት ድንበሩ(1782 እስከ 1822 ዓ.ም) ግንባታው የተጠናቀቀ ታሪካዊ የድንጋይ ካቢ እስከ ዛሬ ድረስ ያለው ትውልድ ይንከባከበዋል ይጎበኛል ለጥናታዊና ምርምር ሥራ ተመርማሪዎች ይጠቀሙበታል፡፡ ዛሬው ትውልድ የአባቶቻችን የጀግንነት አሻራ ያደንቃሉ፣ ይጠቀማሉ፣ ይጠብቃሉ፣ ያለማሉ፣ ለቱሪስት መዳረሻ ያደርጋሉ፤ ከዘርፉም መልካም የሥራ ዕድል በመሆን፤ የህዝብ ተጠቃሚነትንም ይረጋገጣል፤ ለሀገር መልካም ገጽታ ግንባታ ድርሻ ከፍተኛ አድርጎታል፡፡ የንጉስ ሀላላ ድንጋይ ካብ በሰባት የጦር በሮች/ኬላዎች/ በስተምስራቅ ወላይታ ዞን በኩል ሎማ ወረዳ የዚማ ዋሩማ ዳርሚሳሚጣ(በር)፣ በስተደቡብ ጎፋ ዞን በኩል ዲሣ ወረዳ የሾታ ማልዶ ካረ ሚጣ እና በየሊ በር/ሚፃ/፣ በኦሮሚያ ጅማ ዞን በኩል ታርጫ ዙርያ ወረዳ የአባ ኬላ በር/ሚፃ/፣ በሀዲያና ካንባታ ጣንባሮ ዞን በኩል ገና ወረዳ የዳራ በር/ሚፃ/ በወላይታ ዞን በኩል በዛጋዞ ወረዳ ጋራዳ በር/ሚፃ/ና የዛባ በር/ሚፃ/ እና በኮንታ ልዩ ወረዳ በኩል ቃሎ በር/ሚፃ/ ተብሎ በአራሻዎች ይጠበቃል፡፡ በእነዝህ በሮች የዳውሮ ህዝብ ነፃነቱን ያስጠበቀበት ኬላዎች በታሪክ ቅርስነት የሚታወቁ የሚደነቁ ታሪኮች ለትውልድ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገራት ጎበኝዎች ክፍት ተደርጎ ይጠበቃል፡፡ ንጉስ ሀላላ የድንጋይ ካቢ በሰባቱ በሮች በጎጀብና በኦሞ ወንዝ ተከብቦ ያለ አከባቢ ሆኖ በወንዞቹ ህብረተሰቡ የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን ልውውጦችን ከአጎራባች ዞኖች ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንደነበራቸው በግልጽ ይታወቃል፡፡ አርቀው በማሰብ ጥቃቶችን በመተንበይ በአንዳንድ ጉዳዮች አለመግባባት ስከሰት ተንኳሾች ጦርነት እንደሚቀሰቀሱ በመተንበይ የጦረኞች ፈረስ የማይወጣ ድንጋይ ካብ በማስገንባት ከነዝህ መውጫና መግብያ በሮች ከጎሳዎች ሹመት እራሻነት በመስጠት ያስጠብቁ ከነበሩ ታሪካዊ ቦታዎች አንዱ በመሆን ለአድሱ ትውልድና ለቱሪስት መዳረሻነት ባሻገር እንድንመራመርበት ለዘመኑ ትውልድ ያኖረው ታሪክ አሻራና የሚያበረክተው አሰተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡